Blog
11 Apr

ጌትነት ዋለ በ5000ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ

By admin

የቀድሞ የአካዳሚው ሰልጣኝ የነበረው ጌትነት ዋለ በ50ኛው የኢትዮጵያ አትሌትክስ ሻምፒዮና በ5000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ።ጌትነት በቶኪዮ 2020 በርቀቱ ለሜዳሊያ ተስፋ ከተጣለባቸው አትሌቶ ውስጥ አንዱ ነው። አካዳሚው በተለያየ የስፖርት አይነት በርካታ ተተኪዎችን እያፈራ እንደሚገኝ ይታወቃል ።

Read more
Blog
Blog
02 Apr

ከአካዳሚው 5 ተጨዋቾች ለኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ጥሪ ተደረገላቸው

By admin

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በማህበራዊ ሚዲያ ድህረ ገፁ ባሰራጨው መረጃ ሉሲዎቹ ከሚያዝያ 02-05/2013ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን ጋር ለሚያደርጉት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ጥሪ ከተደረገላቸው 26 ተጫዋቾች ውስጥ በአካዳሚው በስልጠና ላይ ከሚገኙት ውስጥ ንግስት በቀለ እና የምስራች ሞገስ ሲገኙበት የአካዳሚውን የአራት አመት የስልጠና ጊዜያቸውን አጠናቀው ክለብ ከተቀላቀሉት ደግሞ አረጋሽ ካልሳ፣ መሳይ ተመስገንና ሲሳይ ገ/ዋህድ ይገኙበታል።

Read more
Blog
21 Mar

አካዳሚው የ2013ዓ.ም የኢትዮጵያ የሴቶች 2ኛ ዲቪዚዮን ፕሪሚየር ሊግ ውድድሩን ከጥሩነሽ ዲባባ ጋር 1ለ1 በመለያየት አጠናቀቀ

By admin

በኢትዮጵያ የሴቶች 2ኛ ዲቪዚዮን ፕሪሚየር ሊግ እየተሳተፈ የሚገኘው የአካዳሚው የሴቶች ከ19 አመት በታች እግር ኳስ ሰልጣኞች ቡድን የሊጉን የመጨረሻ 18ኛ ጨዋታውን መጋቢት 12/2013ዓ.ም ከጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኞ ማዕከል የሴቶች እግር ኳስ አቻው ጋር ጠዋት 2:00 ሰአት ላይ በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም አድርጎ 1ለ1 ተለያየ።

በጫወታው የመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩነሽ ዲባባ የጨዋታ ብልጫ በመውሰድ ጨዋታው ከመጀመሩ ገና በ4ኛው ደቂቃ የመጀመሪያውን ጎል ማስቆጠር የቻሉ ሲሆን ወደ ግብ ክልል በቀላሉ በተደጋጋሚ በመድረስ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት የአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተጫዋቾች በ24ኛው ደቂቃ የፍፁም ቅጣት ምት ቢያገኙም ሳይጠቀሙበት የቀሩ ሲሆን በርካታ የጎል አጋጣሚዎች ቢያገኙም ሳይጠቀሙበት ቀርተው የመጀመሪያው አጋማሽ 1ለ0 ተጠናቋል።

Read more
Blog
13 Mar

አካዳሚው የኮኮብ ጎል አግቢ እና የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነ

By admin

በኢትዮጵያ የሴቶች 2ኛ ዲቪዚዮን ፕሪሚየር ሊግ የተሳተፈው የአካዳሚው የሴቶች ከ19 አመት በታች እግር ኳስ ሰልጣኞች ቡድን ዛሬ በተደረገ የሊጉ የማጠቃለያ የሽልማት ስነስርዓት ላይ የአካዳሚው ተጫዋቾች ንግስት በቀለ በ18 ጨዋታዎች 15 ጎሎችን በማስቆጠር የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ስትሆን በተጨማሪም አካዳሚው በሊጉ ባደረጋቸው 18 ጨዋታዎች በእያንዳንዱ ጨዋታ ኮምሽነሮች በሰጡት የፀባይ ነጥብ ድምር ውጤት ከ10 ክለቦች ውሰጥ አካዳሚው የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

አካዳሚው የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ መሆኑ ተተኪዎችን በስነምግባር ኮትኩቶ ከማሰልጠን አንፃር ጥሩ ስራ እየሰራ መሆኑን አመላካች ነው።

Read more
Blog
07 Mar

አካዳሚው 4 ወርቅ፣2ብር እና 2 የነሀስ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ሻምፒዮናውን አጠናቀቀ

By admin

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው ከየካቲት 23-28/2013ዓ.ም በአሰላ አርንጓዴው ስታዲየም ሲያካሂድ የቆየው 2ኛው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ።

አካዳሚው በሻምፒዮናው 19 ወንድ እና 12 ሴት በድምሩ 31 ሰልጣኞችን ከ18 አመት በታች ውድድሮች ላይ በማሳተፍ 4 ወርቅ፣2ብር እና 2 የነሀስ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ሻምፒዮናውን ሲያጠናቅቅ ለአካዳሚው የተገኙትን ሜዳሊያዎች አኬሎ ኡጁሉ በከፍታ ዝላይ ወርቅ እና በሱሉስ ዝላይ ነሀስ ሲያገኝ ፣ሸሪፍ ረዲ በወንዶች 100ሜትር ወርቅ፣ገመቹ በቀለ በወንዶች 800ሜትር ወርቅ ፣ ታደለ አዱኛ በ400 ሜትር መሰናክል ወርቅ ፣ብርትኳን ተስፋዬ በሴቶች 800ሜትር ብር ፣በወንዶች 2000ሜትር መሰናክል ደግሞ አበበ በላይ እና ሽመልስ ንጉሴ በቅደም ተከተል ብርና ነሀስ በማግኘት የአካዳሚውን ሜዳሊያ መሰብሰብ ችለዋል።

Read more
Blog
06 Mar

አካዳሚው በስፖርት ማማከርና በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ አንደሚገባ ተገለፀ

By admin

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለአሰልጣኞች እና ለስፖርት ባለሙያዎች በስፖርት ማማከር ዘርፍ በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ፕሮጀክት አዘገጃጀት ላይ ለሁለት ቀናት በአዳማ ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።

የአካዳሚው የጥናትና ምርምር ስራዎች ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው የአሰልጣኞች እና ስፖርት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በንድፍ ሀሳብ እና በተግባር የተደገፈ ነበር። የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡን አስተያየት በስልጠናው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በተለይ በሀገራችን ብዙም ባልተለመደ የስፖርት ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ፕሮጀክት አዘገጃጀት ላይ መሆኑ በቀጣይ ማህበረሰብን አሳታፊ የሚያደርግ ስራ ለመስራት ትልቅ መነቃቃትና ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልፀውልናል።

Read more
Blog
01 Mar

ከአካዳሚው ሁለት ብስክሌት ሰልጣኞች ለ15ኛው የአፋሪካ ሻምፒዮና ተመረጡ

By admin

የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከየካቲት 10-13/2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሲያካሂድ በቆየው ለ15ኛው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ የብስክሌት ውድድር ማካሄዱ ይታወሳል።

በውድድሩ የአካዳሚውን የአራት አመት የስልጠና ጊዜያቸውን አጠናቀው በተለያየ ክለቦች ከሚገኙ የቀድሞ ሰልጣኞች እና በመሰልጠን ላይ ከሚገኙ አምስት ሰልጣኞች ለብሄራዊ ቡድን በእጩነት ተይዘው የነበሩ ሲሆን ነገር ግን በመጨረሻው ውጤት በ2012ዓ.ም የስልጠና ጊዜውን አጠናቆ ኢትዮ ኤሌክትሪክን የተቀላቀለው መለሰ ስንታየሁ እና በ2010ዓ.ም ስልጠናዋን አጠናቃ ክለብ የተቀላቀለችው ሰርካለም ታዬ በአዋቂዎች ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው በአህጉር አቀፍ ውድድር እንደሚካፈሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Read more
Blog
31 Jan

የአካዳሚው አትሌቲክስ ሰልጣኞች በ38ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ተሳተፉ

By admin

ዛሬ ጥር 23/2013ዓ.ም በሱሉልታ በተካሄደው አገር አቋራጭ ውድድር አካዳሚው በወጣት ሴቶች 6ኪሎ ሜትር በሁለት ሰልጣኞች እና በወጣት ወንዶች 8 ኪሎ ሜትር በሶስት ሰልጣኞች ተወክሏል ።

ከውድድሩ በኃላ አስተያየታቸውን የሰጡን የአካዳሚው የአትሌቲክስ ስልጠና ክፍል ሀላፊ አሰልጣኝ የሺጥላ ካሳ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአትሌቲክስ ሰልጣኞቻችን በየአካባቢያቸው ባሉበት ቦታ የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ስልጠና እየሰጠን ሲሆን የተወሰኑ ሰልጣኞች በዚህ ሻምፒዮና መሳተፋቸው የውድድር ልምድ እንዲያገኙ ከማስቻሉም ባሻገር ሰልጣኞቹ ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም ትልቅ እድል ፈጥሮልናል ብለዋል።

Read more